ኮይኖች፣ ቲኬቶች እና ወርቆች
ኮይኖች
በእያንዳንዱ ጥቅል ግዢ ተጠቃሚዎች 2 ኮይን እንደ ጉርሻ ያገኛሉ። ለፕሪምየም ተመዝጋቢዎች በግዢ የሚገኝ ሲሆን ይህ የጥያቄ ጨዋታ ተጫዋቾቹ ነጥቦችን እንዲሰበሱ ይረዳቸዋል ይህንንም ወደ ትኬት በመቀየር ለዕለታዊ፣ ለሳምንታዊ፣ ለወርሃዊ እና በየሁለት ወሩ የሚወጡ ዕጣዎችን ለማሸነፍ ይጠቅማቸዋል።
ቲኬቶች
ለፕሪሚየም ተመዝጋቢዎች በጥያቄ ጨዋታዎች የሚሰበሰብ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ እና በየሁለት ወሩ የሚወጡ ዕጣዎች ላይ ለመሳተፍ ይረዳል።
ወርቆች
በጥያቄ ጨዋታዎች ውስጥ ተጠቃሚዎች በጥያቄ ጨዋታ ዉጤት ላይ ተመስርቶ በወርቅ መልክ ሽልማቶችን ያገኛሉ። የሽልማት ሁኔታው፡-
- ከ10 ጥያቄዎች 3ቱን በትክክል በመመለስ፡ 1 ወርቅ
- ከ10 ጥያቄዎች 5ቱን በትክክል በመመለስ፡ 2 ወርቆች
- ሁሉንም 10 ጥያቄዎች በትክክል በመመለስ፡ 5 ወርቆች
ጠቃሚ ማስታወሻ
በፍላጎት ግዢ የሚገዙ ወይም በቦነስ የተገኙ ሳንቲሞች ከ24 ሰዓታት በኋላ የአገልግሎት ጊዜያቸው የሚያበቃ ሲሆን በፍላጎት ግዢ የሚገዙ ወይም በቦነስ የተገኙ ወርቆች ከ7 ቀናት በኋላ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃል።
በጥያቄና መልስ የነጥብ አያያዝ
- በድረገ-ገፅ ወይም በሚኒ-አፕ ላይ ለሚጫወቱ ነጥብ አያያዝ
- ተጠቃሚዎች ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስ ለመስጠት 10 ሰከንድ ይሰጣቸዋል። የተዘለሉ ጥያቄዎች እንደ ተሳሳተ ምላሽ ይቆጠራሉ እና ምንም ነጥብ አይኖራቸውም።
- በጥያቄ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቾች ለእያንዳንዱ ትክክለኛ ምላሽ 10 ነጥብና ተጨማሪ የጉርሻ ወርቅ እንደመለሱት የጥያቄ ብዛት ያገኛሉ፡፡ ከ 3 እስከ 4 ጥያቄዎች በትክክል ሲመልሱ 1 ወርቅ፤ ከ5 እስከ 9 ጥያቄዎችን በትክክል ሲመልሱ 2 ወርቆችን እንዲሁም ሁሉንም 10 ጥያቄዎችን በትክክል ሲመልሱ 5 ወርቆችን ያገኛሉ።
- በተጨማሪም ተጫዋቾች ለፍጥነታቸው እና ለጥያቄዎች ምላሽ ቅልጥፍና የጊዜ ጉርሻ ተጨማሪ ነጥብ አላቸው፡፡
- በተከታታይ ትክክለኛ ምላሽ መስጠትም ተጨማሪ ጉርሻ ያስገኛል፡፡ 3 ተከታታይ ጥያቄዎችን በትክክል የመለሱ ተጫዋቾች የ10 ነጥብ ጉርሻ ያገኛሉ። ለ6 ተከታታይ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ከሰጡ ይህ ጉርሻ ወደ 30 ነጥብ ያድጋል እንዲሁም ለ9 ተከታታይ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልሶች ከሰጡ ነጥቡ ወደ 50 ይጨምራል። ይህ ተከታታይ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት የሚገኝ ጉርሻ ተግባራዊ የሚሆነው ተጫዋቾች ትክክለኛውን መልስ ሲመልሱ ብቻ ሲሆን ተጠቃሚው ትክክለኛውን መልስ ካላገኘ የጊዜ ጉርሻ አያገኝም።
- በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ለሚጫወቱ ነጥብ አያያዝ
- በፅሁፍ መልዕክት ለጥያቄና መልስ በመሳተፍ ጉርሻዎችን ለማግኘት Ok ወደ 129 ይላኩ!
- ለእያንዳንዱ ትክክለኛ መልስ ተሳታፊዎች 500 ነጥብ ያገኛሉ።
- ተጠቃሚዎች 2 ምርጫዎች ብቻ ያላቸውን ጥያቄዎች ይቀበላሉ ከዚያም 1 ወይም 2 በመላክ መመለስ ይችላሉ።
- ተጠቃሚዎች በፅሁፍ መልዕክት ለጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ለእያንዳንዱ ወደ 129 ለተላክ መልዕክት 2 ብር ይከፍላሉ፡፡
- በፅሁፍ መልዕክት ጨዋታ ውስጥ በተከታታይ በመመለስ የሚገኝ ጉርሻ ወይም የጊዜ ጉርሻ አይኖርም።
የሽልማት አሰጣጥ ሂደት
ፈጣን ሽልማቶች
- የዕድል ጨዋታ ለነጻ ተጠቃሚዎች፡ የሞባይል ዳታ፣ የድምጽ ጥቅል እና የአየር ሰአት
- የዕድል ጨዋታ ለፕሪሚየም ተጠቃሚዎች፡ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የሞባይል ዳታ፣ የድምጽ ጥቅል እና ስማርት ስልኮች
- ተጠቃሚዎች የጥቅል ሽልማት ሲያሸንፉ ወዲያውኑ ወደ ስልካቸው ይላካል።
ሌሎች ሽልማቶች
- ተጠቃሚዎች በሰበሰቡት የነጥብ ብዛት መሰረት ሽልማቶችን ለማሸነፍ ብቁ ናቸው። እነዚህ ነጥቦች ወደ ቲኬቶች ተቀይረው ተጠቃሚዎች በዕጣ ይመረጣሉ።
- በእለታዊ እና ሳምንታዊ እጣዎች ላይ ለመሳተፍ ተጠቃሚዎች ከ10,000 እስከ 20,000 ነጥቦች ሊኖራቸው ይገባል።
- እንደ ሽልማት የሚቀርቡት የስማርት ስልኮች ብዛት እና አይነት በማስታወቂያ ቆይታ ጊዜ ውስጥ ሊለዋወጡ ይችላሉ።
- ተሸላሚው ለኤሌክትሪክ እና ከባጅጅ ተሽከርካሪ መመዝገቢያ ጋር ተያይዞ የስም ለውጥ እና ተዛማጅ የስራ ሂደት ክፍያዎችን አሸናፊው ይሸፍናል። ኢትዮ ቴሌኮም ሽልማቱን መሸለሙን ካረጋገጠ በኋላ አሸናፊው እነዚህን ወጪዎች መሸፈን አለበት።
ስለ ኢትዮ130 lucky slot ማብራሪያ ለማግኘት 👉 https://bit.ly/4dckxdb