ኢትዮ 130 Lucky Slot
የኩባንያችንን 130 ዓመታት ክብረ በዓል ከእናንተ ከውድ ደንበኞቹ ጋር በልዩ ስጦታዎች
Ethio130 Lucky Slot ጨዋታ የአየር ሰዓት በመሙላትና የቴሌብር አገልግሎቶችን በመጠቀም ተሸላሚ ይሁኑ!
እስከ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ
አገልግሎታችንን ይጠቀሙ፤
የድርሻዎን ይውሰዱ!
የስጦታ ዝርዝር
የስጦታዎቹ መውጫ ቀን |
የስጦታ ዓይነት |
ብዛት |
---|---|---|
ዕለታዊ |
20 ሺህ ብር |
180 |
ሳምንታዊ |
ስማርት ስልኮች |
70 |
50 ሺህ ብር |
48 |
|
በየወሩ |
ባጃጅ |
3 |
በየ2 ወሩ |
የኤሌክትሪክ መኪና |
3 |
ሌሎች ፈጣን የሞባይል ጥቅል ስጦታዎችን በየቀኑ ያገኛሉ!
ለመመዝገብ
- *131# በመደወል
- በቴሌብር ሱፐርአፕ የፊት ገፅ ላይ Ethio130 Lucky Slot መተግበሪያ
- https://ethiotel130-megapromo.et/ ይጎብኙ
- OK ብለው ወደ 131 ይላኩ
የአገልግሎት ክፍያ በቀን 3 ብር
የብቁነት መስፈርቶች
ለጨዋታው ብቁ ለመሆን ከ 10 ብር ጀምረው የአየር ሰዓት ይግዙ!
እንዲሁም በቴሌብር
- 5 ብር እና ከዚያ በላይ የሞባይል ጥቅል ይግዙ
- 10 ብር እና ከዚያ በላይ የኢትዮ ቴሌኮም ድህረ ክፍያ ይፈፅሙ
- 50 ብር እና ከዚያ በላይ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ይክፈሉ
- 100 ብር እና ከዚያ በላይ ለግብይት ይክፈሉ
- 250 ብር እና ከዚያ በላይ ገንዘብ ይላኩ
- 300 ብር እና ከዚያ በላይ በወኪሎች ገንዘብ ወጪ ያድርጉ
- 500 ብር እና ከዚያ በላይ በወኪሎች ገንዘብ ያስገቡ
- 500 ብር እና ከዚያ በላይ ለነዳጅ ይክፈሉ
- 1,000 ብር እና ከዚያ በላይ ያስተላልፉ
ስለጨዋታ
ኮይኖች
- ጨዋታው የነፃ ተጠቃሚዎችን እና ፕሪሚየም ተጠቃሚዎችን/ተመዝጋቢዎችን ለመለየት የብር እና የወርቅ ኮይኖችን ይጠቀማል፡፡
- የብር ኮይን የነፃ ተጠቃሚዎች በብራማው ማሽን እንዲጫወቱ ያስችላል፡፡ የወርቅ ኮይን የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ደግሞ በወርቃማው ማሽን እንዲጫወቱ ያስችላል፡፡
- የአየር ሰዓት ሲሞሉና ክፍያዎን በቴሌብር ሲፈፅሙ በገንዘብ መጠኑ መሰረት ያደረገ የብር ወይም የወርቅ ኮይኖችን ያገኛሉ፡፡
- የ10 ብር እና ከዚያ በላይ የአየር ሰዓት ሲሞሉ በሞሉት የ10ብር አየር ሰዓት ልክ 1 ኮይን + 1 ሳምንታዊ ቲኬት ያገኛሉ፡፡
- የነፃ ተጠቃሚዎች / የብር ኮይን ተጠቃሚዎች/ ከ10 ብር ጀመሮ እስከ 49 (ከ50 ብር በታች) አየር ሰዓት በቴሌብር አማካይነት ሲሞሉ ተጨማሪ 2 የብር ኮይኖች + 2 ሳምንታዊ ቲኬት ያገኛሉ፡፡
- የነፃ ተጠቃሚዎች / የብር ኮይን ተጠቃሚዎች/ ከ50 ብር በላይ የአየር ሰዓት በቴሌብር አማካይነት ሲሞሉ ተጨማሪ 2 የወርቅ ኮይኖች + 2 ሳምንታዊ ቲኬት ያገኛሉ፡፡
- የኢትዮ-ቴሌኮም ደንበኞች በኢትዮ130 ላኪ ስሎት ሲመዘገቡ እና ደንበኝነታቸውን ሲያድሱ 3 የወርቅ ኮይኖች በየቀኑ ያገኛሉ፡፡ በወርቃማው ማሽን ተጫውተው እስከ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና የመሸለም ዕድል ያገኛሉ፡፡
- እያንዳንዱ የመጫወቻ ኮይን ከተሰጠበት (ደንበኞች ካገኙበት) ቀን ጀምሮ ለ7 ቀናት ብቻ በማሽኑ እንዲጫወቱ ያስችላል፡፡
ግብይቶችን በቴሌብር ሲፈጽሙ የሚያገኙት ኮይኖች እና ቲኬቶች፤
የነፃ ተጠቃሚዎች በቴሌብር አማካይነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግብይቶችን ሲፈጽሙ ሳምንታዊ ቲኬት እና የብር ኮይኖች ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ስጦታ የሚያስገኙ ግብይቶችን ሲፈጽሙ በወርቅ ማሽን ተጫውተው ትልልቅ ሽልማቶችን ማሸነፍ የሚያስችሉ የወርቅ ኮይኖችን ያገኛሉ፡፡
ተጨማሪ ኮይኖችን በፍላጎት ስለመግዛት
ተጨማሪ ጨዋታ በፍላጎት ለመግዛት በ1 ብር 1 ኮይን፤ በ3 ብር 4 ኮይን እንዲሁም በ5 ብር 7 ኮይን መግዛት ይችላሉ፡፡
ስለመጫወቻ ማሽኖች (ስሎትስ)
- በመጫወቻ ድረ-ገፁ ላይ ሁለት ማሽኖች ማለትም አንድ ብራማ እና አንድ ወርቃማ ማሽኖች አሉ፡፡
- የወርቃማ ማሽኑን ለመቀጠም ለአገልግሎቱ በመመዝገብ የፕሪሚየም ተጫዋች መሆን ይኖርብዎታል፡፡
- የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች በሁለቱም ማሽኖች ላይ መጫወት ይችላሉ፡፡
- ሁሉም ደንበኞች (ነፃ ተጠቃሚ እና ተመዝጋቢ) በመጫወቻ ማሽኖቹ ሲጫወቱ ካላቸው ጠቅላላ ኮይን 1 ኮይን ተቀናሽ ይሆናል፡፡
ቲኬቶች
- ጨዋታው ሁለት ዓይነት ቲኬቶች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም የሳምንታዊ ዕጣ ቲኬት እና ፕሪሚየም ቲኬት ናቸው፡፡
- የሳምንታዊ ዕጣ ቲኬት የአየር ሰዓት ሲሞሉ እንዲሁም የቴሌብር ክፍያዎችን ሲፈፅሙ የሚያገኙት ሲሆን በየሳምንቱ 50ሺህ ብር በዕጣ የሚሸለሙበት ቲኬት ነው፡፡
- ፕሪሚየም ቲኬት በወርቃማ መጫወቻው ላይ በመጫወት የሚያገኙት ቲኬት ነው፡፡
- የፕሪሚየም ቲኬቶች ለወርሃዊ ወይም በየሁለት ወር ለሚካሄዱ የባጃጅ እና የዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችልዎት ነው፡፡
የማስታወስ ጨዋታ
- በዚህ ጨዋታ በውስጡ ያሉትን የተሰወሩትን ካርዶች/ምስሎች ከተመሳሳያቸው ጋር በማጣመር የሚጫወቱት ክህሎትን የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን ባገኙት ጥምር ምስል ልክ ቲኬቶችን የሚያገኙበት ጨዋታ ነው፡፡
- ጨዋታውን ማግኘት የሚቻለው በወርቃማው መጫወቻ ከተጫወቱ በኋላ ሲሆን በመጨረሻም ያሸነፉትን የቲኬት መጠን እና በወርቃማው መጫወቻ የተሸለሙትን ሽልማት ይመለከታሉ፡፡
- ይህን ጨዋታ በመጠቀም በተቻለ መጠን ብዙ ቲኬት በመሰብሰብ በየወሩ እና በየሁለት ወሩ በሚደረጉ ታላላቅ ዕጣዎች ላይ በተሻለ የማሸነፍ ዕድል እንዲኖርዎ ያደርገዎታል፡፡
ዝርዝር ሽልማቶች
- የብር ኮይኖችን ተጠቅመው ፈጣን ሽልማቶችን ማለትም የሞባይል ጥቅሎችን እና የሳምንታዊ ዕጣ ትኬቶችን በብራማ መጫወቻ ማሽን ውስጥ ማሸነፍ ይችላሉ፡፡
- የወርቅ ኮይኖችን ተጠቅመው ፈጣን ሽልማቶችን ማለትም የሞባይል ጥቅሎችን፣ የሳምንታዊ ዕጣ ትኬቶችን፣ ስማርት ስልኮችን እና 20 ሺህ ብር በወርቃማ መጫወቻ ማሽን ውስጥ ማሸነፍ ይችላሉ፡፡
- በየሳምነቱ የዘመናዊ ስማርት ስልኮች አሸናፊዎች ይለያሉ፡፡ በተጨማሪም የ50 ሺህ ብር ሁለት አሸናፊዎች በየሳምንቱ በዕጣ የሚለዩ ሲሆን የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች እና ከፍተኛ ስጦታ የሚያስገኙ ግብይቶችን በቴሌብር የፈፀሙ ነፃ ተጠቃሚዎች በዕጣው ውስጥ ለመካተት ብቁ ናቸው፡፡
- እስከ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በየ2 ወሩ አንድ የባጃጅ እና የመኪና አሸናፊዎች ይኖራሉ፡፡
አገልግሎቱን ለማቋረጥ ከፈለጉ STOP ወደ 131 ይላኩ!