ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመሠረተልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንን ስትራቴጂ እውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን፣ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ በመደረግ ላይ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥረት በመደገፍ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የመመዝገቢያ መሳሪያዎችን በመግዛት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላቱን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን የምዝገባ ስራ በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ኩባንያችን የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ከማከናወን ባሻገር ደንበኞች የህትመት ጥያቄ/ትእዛዝ በቴሌብር ሱፐርአፕ በኦንላይን በማከናወን እና ክፍያ በመፈጸም እንደምርጫቸው ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘሩት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 63 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት/ የካርድ መቀበያ ቦታዎች መታወቂያ ካርዳቸውን መረከብ የሚችሉበትን አሰራር በይፋ አስጀምሯል፡፡
ይህም አገልግሎት ደህንነቱ አስተማማኝ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ካርድ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት መተግበሪያ ወይም በድረገጽ https://teleprint.fayda.et/ በመግባት፣ የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN) በማስገባት፣ በአጭር ጽሑፍ የሚላከውን የማረጋገጫ መለያ ኮድ በማስገባት፣ የአገልግሎት ፍጥነት፣ ካርድ የመረከቢያ ቀን እና ቦታ እንደፍላጎታቸው መምረጥ ይችላሉ፡፡
የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ደንበኞች በተለያየ የህትመት ማድረሻ ፍጥነት አማራጮች (delivery time) ማለትም ለመደበኛ በ7 የሥራ ቀናት (345 ብር)፣ ለፕሪሚየም በ2 የስራ ቀናት (600 ብር) እና ለኤክስፕረስ አስቸኳይ (800 ብር) በቀላሉ በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡
የመታወቂያ ህትመቱ አገልግሎቱ ዘመናችን በደረሰበት የመጨረሻ የህትመት ቴክኖሎጂ በላቀ የህትመት ጥራት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፣ በቀላሉ የማይጫጫር፣ ቀለሙ የማይለቅ እና ሳይበላሽ እስከ 10 አመታት የሚደርስ የአገልግሎት እድሜ ያለው ነው፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮን እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስን ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ የአነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማእከሎቻችን ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማእከሎቻችን ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፡፡
ተ.ቁ | የአገልግሎት ማዕከል |
---|---|
1 | ባምቢስ አገልግሎት ማዕከል |
2 | ጌጃ ሰፈር የአገልግሎት ማዕከል |
3 | ካዛንቺስ አገልግሎት ማዕከል |
4 | ልደታ አገልግሎት ማዕከል |
5 | መስቀል ፈላወር አገልግሎት ማዕከል |
6 | ስታዲየም የሃ ህንፃ አገልግሎት ማዕከል |
7 | ተክለሃይማኖት አገልግሎት ማዕከል |
8 | ቴሌ ጋራጅ |
9 | ውሃልማት አገልግሎት ማዕከል |
10 | አያት አደባባይ አገልግሎት ማዕከል |
11 | አያት ሲኤምሲ-ፀሃይ ሪል እስቴት አገልግሎት ማዕከል |
12 | ቦሌ አራብሳ አገልግሎት ማዕከል |
13 | ቦሌ መድኃኒአለም አገልግሎት ማዕከል |
14 | ቦሌ ሚካኤል አገልግሎት ማዕከል |
15 | ቦሌ ሚሊንየም አገልግሎት ማዕከል |
16 | ቦሌ ኖቪስ ካዝ ሆቴል |
17 | ቦሌ ቴሌ/ ሸገር ህንፃ ፊትለፊት |
18 | ፊጋ የአገልግሎት ማዕከል |
19 | ገርጂ የአገልግሎት ማዕከል |
20 | ሀያሁለት ጐላጉል አገልግሎት ማዕከል |
21 | (መገናኛ አደባባይ) - ደራርቱ ሕንፃ |
22 | ሳሚት 72 የአገልግሎት ማዕከል |
23 | 4 ኪሎ-ቱሪስት አገልግሎት ማዕከል |
24 | 6 ኪሎ አገልግሎት ማዕከል |
25 | ፈረንሳይ አገልግሎት ማዕከል |
26 | ጉርድሾላ አገልግሎት ማዕከል |
27 | ኮተቤ መሳለሚያ አገልግሎት ማዕከል |
28 | መገናኛ- አማር ደስታ ህንፃ አገልግሎት ማዕከል |
29 | ሽሮሜዳ አገልግሎት ማዕከል |
30 | ወሰን አገልግሎት ማዕከል |
31 | የካ አባዶ አገልግሎት ማዕከል |
32 | አቃቂ አለም ባንክ አገልግሎት ማዕከል |
33 | አቃቂ በሰቃ አገልግሎት ማዕከል |
34 | አልማዝዬ ሜዳ አገልግሎት ማዕከል |
35 | ቦሌ ቡልቡላ አገልግሎት ማዕከል |
36 | ጎፋ ሶፊያ የገበያ ማዕከል አገልግሎት ማዕከል |
37 | ሃና ማሪያም አገልግሎት ማዕከል |
38 | ቃሊቲ (አቢሲኒያ ባንክ ፊት ለፊት)አገልግሎት ማዕከል |
39 | ቂርቆስ አገልግሎት ማዕከል |
40 | ንፋስ ስልክ አገልግሎት ማዕከል |
41 | ሳሪስ አገልግሎት ማዕከል |
42 | ቱሉ ዲምቱ አገልግሎት ማዕከል |
43 | አለምገና አገልግሎት ማዕከል |
44 | አየርጤና አገልግሎት ማዕከል |
45 | ቤቴል አገልግሎት ማዕከል |
46 | ጀሞ 1 አገልግሎት ማዕከል |
47 | ለቡ ቫርኔሮ አገልግሎት ማዕከል |
48 | ሳርቤት አገልግሎት ማዕከል |
49 | ጦርሃይሎች ቀጠና 2 የአገልግሎት ማዕከል |
50 | ወለቴ አገልግሎት ማዕከል |
51 | አዲሱ ገብያ አገልግሎት ማዕከል |
52 | አራዳ ጊዮርጊስ አገልግሎት ማዕከል |
53 | አሸዋ ሜዳ አገልግሎት ማዕከል |
54 | አስኮ አገልግሎት ማዕከል |
55 | አውቶብስ ተራ አገልግሎት ማዕከል |
56 | ቡራዩ አገልግሎት ማዕከል |
57 | እንቁላል ፋብሪካ - ታደሰ ቸኮል አገልግሎት ማዕከል |
58 | ፋይናንስ ሸጎሌ አገልግሎት ማዕከል |
59 | ቀጨኔ አገልግሎት ማዕከል |
60 | ኮልፌ አገልግሎት ማዕከል |
61 | መርካቶ ምዕራብ አገልግሎት ማዕከል |
62 | መርካቶ ሰባተኛ አገልግሎት ማዕከል |
63 | መሳለሚያ ሸዋ ፀጋ አገልግሎት ማዕከል |
ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም