የፀሐይ ኃይል
የቤት ውስጥ የፀሐይ ኃይል አቅርቦት
የቤት ውስጥ የፀሐይ ኃይል አቅርቦት፤ ለመኖሪያ ቤት አማራጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚያስችል የፀሐይ ኃይል አቅርቦት ሲኾን፤ ዘላቂ፣ አስተማማኝና ተመጣጣኝ እንዲኹም እስከ 400 ዋት ድረስ አቅም ያለው የኤልክትሪክ ኃይልን ይሰጣል፡፡
የፀሐይ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይር፤ የተለወጠውን ኤሌክትሪክ ኃይል ወዲያውኑ ጥቅም ላይ የሚያውል ወይም ለዚህ አገልግሎት ታስቦ በተነደፈው በባትሪ ውስጥ ኃይል የሚያከማች!
የተከማቸውን ኃይል በተለያዩ የቤት ውስጥ አገልግሎቶች፡-
• መብራት በሌላቸው አካባቢዎች፣
• የስልክ ባትሪ ለመሙላት፣
• ለሬዲዮና ቲቪ መጠቀም ያስችላል፡፡
የኃይል እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች፤
የኤልክትሪክ ወጪን የሚቀንስ፤
ሥነ መዋቅር
ባትሪ
ሞጁል
ምሰሶ
ባለ 120 ዋት
75,437.50
ብር
- 120ዋ ሶላር ፓኔል
- 65Ah ጄል ባትሪ
- 10A mppt መቆጣጠሪያ፣ ከGPRS ጋር
- 300ዋ ኢንቨንተር
- ምሰሶ ወይም የጣሪያ መደርደሪያ
- የPV ገመድ፣ 5 ሜትር
- የRVV ገመድ፣ 10 ሜትር
- 5ዋ LED አምፖል፣ 3 ፍሬ
- የመብራት ማቀፊያ፣ 3 ፍሬ
- ስዊች፣ 3 ፍሬ
ባለ 200 ዋት
109,628
ብር
- 200ዋ ሶላር ፓኔል
- 100Ah ጄል ባትሪ
- 20A mppt መቆጣጠሪያ፣ ከGPRS ጋር
- 600ዋ ኢንቨንተር
- ምሰሶ ወይም የጣሪያ መደርደሪያ
- የPV ገመድ፣ 5 ሜትር
- የRVV ገመድ፣ 10 ሜትር
- 5ዋ LED አምፖል፣ 3 ፍሬ
- የመብራት ማቀፊያ፣ 3 ፍሬ
- ስዊች፣ 3 ፍሬ
ባለ 400 ዋት
181,250.00
ብር
- 400ዋ፣ ሁለት 200ዋ ሶላር ፓኔል
- 200Ah ጄል ባትሪ
- 40A mppt መቆጣጠሪያ፣ ከGPRS ጋር
- 1000ዋ ኢንቨንተር
- ምሰሶ ወይም የጣሪያ መደርደሪያ
- የPV ገመድ፣ 5 ሜትር
- የRVV ገመድ፣ 10 ሜትር
- 5ዋ LED አምፖል፣ 3 ፍሬ
- የመብራት ማቀፊያ፣ 3 ፍሬ
- ስዊች፣ 3 ፍሬ
ደንብና ኹኔታዎች
•የአከፋፈል መንገድ በቅድመ ክፍያና በአንድ ጊዜ ክፍያ ነው።
• በደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር በኩል ለሽያጭ መገኘት አለበት።
• ደንበኛው በረጅም ጊዜ ክፍያ ሥርዐት መሳርያውን የሚገዛ ከሆነ፤ M2M ሲምን ከጥቅል ጋር መግዛት አለበት።
• የM2M ሲም ከጥቅልና ከመሳርያው ዋጋ ጋር የተለያየ ነው።
• ደንበኞች በቀጥታ ኹሉንም ክፍያ ፈጽመው የሚገዙ ከኾነ (ሙሉውን ዋጋ በአንድ ጊዜ ከፍለው)፤ M2M ሲምና ጥቅል መግዛት አይጠበቅባቸው፡፡
• የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ተቋማትና ግለሰቦች ወይም አጋሮች በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ማመቻቸት አለባቸው።
• ኢትዮ ቴሌኮም የመሳርያውን አጠቃላይ ዋጋ በቫት ይሰበስባል።
• ከሲምና ጥቅል ጋር የተያያዘ ገቢ የኢትዮ ቴሌኮም ብቻ ነው።
• በሁለቱ አጋር ድርጅቶች ስምምነት መሠረት የገቢ ድርሻ ዋጋ ይቀየራል።
• ኹሉም ክፍያዎች ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቁ በኋላ፣ ከደንበኛ-ተኮር የሶላር መሳርያዎች ጋር የተገናኘው M2M ግንኙነት ይቋረጣል።
• የM2M ሲም ከጥቅል ዋጋና ከመሳርያው ዋጋ ጋር የተለያየ ነው።