የጨረታ ማብቂያ ቀን ለአንድ ሳምትን መራዘሙን ስለማሳወቅ::

ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና ጄኔሬተሮች ከታህሳስ 25 ቀን 2017 እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቅያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም የጨረታ ማብቂያ ቀን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለአንድ ሳምንት ተራዝሞ የመጨረሻው ቀን ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እሰከ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከአፍሮ ቴንደር ዶትኮም (www.afrotender.com)፣ ከቱመርካቶ (www.2Merkato.com) ወይም ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratender.Com.et) ድህረገጾች ብር 500.00 (አምስት መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  2. ንብረቶቹን አቃቂ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ – አርብ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ 10% (አስር ከመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው አቃቂ በሚገኘው የኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕቃ ግምጃቤት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  5. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡            

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives