የጨረታ ማስታወቂያ

 

                  የጨረታ ቁጥር WAAZ/01/2017

ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባኒያዉ አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ በመጠኑ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች (ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣…ካዝናዎች)፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የአልሙኒዬም ቁርጥራጮች፣ ቤርሚሎች  እንዲሁም ያገለገሉ የእንጨት ምሰሶዎች ባሉበት ሁኔታ ለህጋዊ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከየካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከየካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ድረስ ከኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን እንቁላል ፋብሪካ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሺያል ኮምፕሌክስ ቢሮ ቁጥር 801 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረበዉን የተለያዩ በመጠኑ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች (ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ …ካዝናዎች) አስኮ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከል ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ፣ ለካዝና አዲሱ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከል፤ እንዲሁም ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የአልሙኒዬም ቁርጥራጮች፣ ቤርሚሎች እንዲሁም ያገለገሉ የእንጨት ምሰሶዎችን ደግሞ አስኮ ጫረታ አለፍ ብሎ አስኮ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በሚገኘዉ ኢትዮ ቴሌኮም ሞባይል ጣቢያ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝና ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ፣በመገኘት ዘወትር በስራ ቀናት ከየካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ከረፋዱ 4፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናዉ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) መሆን አለበት፡፡

  1. ተጫራቾች የተለያዩ ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን ማለትም በመጠኑ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች (ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣…ካዝናዎች)፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የአልሙኒዬም ቁርጥራጮች፣ ቤርሚሎች እንዲሁም ያገለገሉ የእንጨት ምሰሶዎች በጥቅል (ሎት) የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ፎርም መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በአይነት መደብ (በጥቅል) የሚገዙትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን የሚያሳይ የዋጋ ማስገቢያ ቅጽ/ፎርም፡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ፤የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ፡ የተጫራቾች አድራሻ መግለጫን በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን እንቁላል ፋብሪካ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሺያል ኮምፕሌክስ ቢሮ ቁጥር 801 ከየካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ከረፋዱ 4፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን እንቁላል ፋብሪካ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሺል ኮምፕሌክስ ቢሮ ቁጥር 801 መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም በመክፈቻው ቀንና ቦታ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ ካልተገኙ እንደተገኙ ተቆጥሮ በተገኙት ተጫራቾች ፊት ያቀረቡት የጨረታ ሠነድ ይከፈታል፡፡ 

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives