ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን

የእንስሳት አያያዝን የሚያዘምን እና የሚገኙበት ቦታ ዲጂታል በመሆነ መልኩ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን ይህ ዘመናዊ ሶሉሽን ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የእንስሳትን ደህንነት ለማሻሻል በተለይም የእንስሳት ባለቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ የኢንተርኔት ቁስ (IoT)፣ ክላውድ ቴክኖሎጂን እና የሞባይል ኮኔክቲቪቲን በመጠቀም አርሶ አደሮች እና እንሰሳት አርቢዎች በቀላሉ እንስሳቶቻቸውን መከታተል፣ ያሉበትን ቦታ መለየት እና የጤና ሁኔታቸውን መገምገም እንዲችሉ እንዲሁም ውጤታማነትን፣ ደህንነትን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እንዲያረጋግጡ ከፍተኛ ፋይዳ አለው::
የኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል የእንስሳት መከታተያ ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን የሚከተሉትን ዲጂታል እንስሳት መከታተያ መሳሪያዎችን ያካተተ ነው።
• የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ መለያዎች/ታግ (RFID Tags): በእንስሳት በጆሮ ላይ የሚገጠሙ መለያዎች አማካኝነት ወሳኝ መረጃዎችን የሚመዘግቡ አነስተኛ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ልዩ የእንስሳት ዝርዝር መለያዎችን፣ ቀለማቸውን፣ ጾታቸውን፣ የተወለዱበትን ቀንና ዕድሜያቸውን ይመዘግባሉ።
• በጂፒኤስ የታገዙ የራዲዮ ፍሪኩዌንሲ መለያዎች/ታግ (GPS-integrated RFID Tags): የእያንዳንዱን እንስሳት መገኛ ቦታን በቀላሉ ለመከታተል ወይም ለመለየት ያስችላሉ።
• የጂፒኤስ ቺፕሴት (GPS Chipsets)፡ ስለእንስሳቱ ሁለንተናዊ መረጃን መስጠት የሚያስችል ራቅ ባሉ አካባቢዎች ቢጓዙ ወይም ቢጠፉ የት እንደሚገኙ ለማወቅ በቀላሉ ተከታትሎ መረጃ የማቅረብ አቅም ያለው እና ሁለንተናዊ የመረጃ ስብስብ ማለትም RFID፣ GPS እና chipset ቴክኖሎጂን በማጣመር እንደላቀ አማራጭ የሚያገለግል ነው። ይህ መረጃ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ፕላትፎርም ከሲስተም ጋር ተቀናጅቶ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በድረገጽ በታገዘ የመድን ስርዓት (web-based insurance system) እና ለመስክ ሰራተኞች ወይም የድርጅት ወኪሎች በተዘጋጀ የሞባይል መተግበሪያ ተደራሽ የሚሆን ነው።
ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች
• የቁም እንስሳት ቅጽበታዊና የሙሉጊዜ ክትትል፡ አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት የእንስሳት ሀብታቸው ያሉበት ቦታና ደረጃን በመከታተል የእንስሳት አያያዝን ለማሻሻል እና የሚደርስባቸውን ኪሳራ ለመቀነስ ይችላሉ።·
• ቀላል/ምቹ ለሆነ የፋይናንሺያል አካታችነት፡– በሶልሽኑ በተረጋገጠ መረጃ በመታገዝ ባንኮች እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንስሳቱን እንደ መያዣ በመቀበል የብድር እና የመድን ዋስትና አገልግሎትን ለመስጠት አመኔታ እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል።·
• የተሳለጠ የኢንሹራንስ ይገባኛል ጥያቄ፡– ሶሉሽኑ የኢንሹራንስ ይገባኛል ጥያቄ ሂደቱን ስለሚያቃልል እና ስለሚያፋጥን በካሳ አከፋፈል ረገድ የሚከሰት አለመግባባትን እና ማጭበርበርን ይቀንሳል
• በመረጃ/ዳታ የታገዘ ውሳኔ ለመስጠት፡ የተሰበሰበው መረጃ/ዳታ ለፖሊሲ ቀረጻ እና ሀብት ድልድል ጠቃሚ ዕይታዎችን በመስጠት በእንስሳት ዘርፍ ለዘላቂ ልማት ዕገዛ ያደርጋል።·
• ከቴሌብር የክፍያ ስርዓት ጋር ትስስር ያለው፡– ከኢትዮ-ቴሌኮም የቴሌብር የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ጋር ሙሉ ትስስር ስላለው ቀላል፣ምቹና ፈጣን ግብይት እንዲኖር ያስችላል። ·
• በቴሌክላውድ የታገዘ እና በየጊዜው ሊሻሻል የሚችል፡– ኢትዮ ቴሌኮም ይህ ሶሉሽን በቀጣይነት ለወደፊት በየጊዜው ሊሻሻል በሚችል መልኩ በማዘጋጀት ቴክኖሎጂውን ለማቅረብ ችሏል።ይህ ሶሉሽን ለእንስሳት ሀብት ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ግስጋሴ ላይ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገበሬዎችን እና ሌሎች እንስሳት አርቢዎችን የሚያበረታታ፣ የእንስሳት እርባታ አያያዝን የሚያዘምን እና የፋይናንስ አካታችነትን የሚያረጋግጥ ነው። ይህ ኢንሼቲቭ የግብርና ዘርፉን ከማዘመን ባሻገር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ጉዞ በማፋጠን በማደግ ላይ ያለውን የሀገራችንን የገጠር ኢኮኖሚ ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል።