ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጂን ባሌ ሮቤ እና በደቡብ ምስራቅ ሪጅን አሰላ ከተሞች የ5ጂ እንዲሁም በ114 የሪጅኖቹ ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀመረ!

በሀገራችን ቀዳሚ የቴሌኮም እና ዲጂታል አገልግሎቶች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በባሌ ሮቤና አሰላ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያችን በደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጅኖች በሚገኙ 114 ከተሞች ዘመናዊውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የአካባቢው ማህበረሰብ ከኮኒክቲቪቲ ባሻገር የዲጂታል እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲችሉ በማድረጉ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ኢትዮ ቴሌኮም የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ጥረት አካል ሲሆን፣ በመላ ሀገሪቱ አስተማማኝ፣ እንከን አልባ እና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ ለአዳዲስ ፈጠራዎች እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አዳዲስ ዕድሎችን ይከፍታል።

5ጂ አገልግሎት በባሌ ሮቤ እና አሰላ ከተሞች!

ኩባንያችን በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ. በ2022 ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የ5ጂ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ በመላ ሀገሪቱ ወደሚገኙ ከተሞች እያስፋፋ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ድረስ ባሌ ሮቤና አሰላን ጨምሮ በ16 ትላልቅ ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ፣ በቢሾፍቱ እና በጅማ፣ በደሴና ኮምቦልቻ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት አዲስ በተቋቋመው በደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጂን ባሌ ሮቤ እና በደቡብ ምስራቅ ሪጅን አሰላ ከተሞች ከተሞች የተጀመረው የ5ጂ አገልግሎት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያን የመጪው ጊዜ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማስቻል እንዲሁም የዲጂታል እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለመጨመር ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።

የ5ጂ አገልግሎት በባሌ ሮቤ ከተማ

በባሌ ሮቤ ከተማ በመከናወን ላይ የነበረውን የ5ጂ ኔትወርክ ዝርጋታ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ፣ አገልግሎቱ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ለማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤ እነርሱም፡-
• ዋቆ ጉቱ አደባባይ፣
• ሮቤ ኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ (ነባሩ)፣
• ባሌ ዞን ትምህርት ቢሮ፣
• ሮቤ ቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ እና
• መደወላቡ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ ናቸው፡፡

የ5ጂ አገልግሎት በአሰላ ከተማ

በተጨማሪም በአሰላ ከተማ በመከናወን ላይ የነበረውን የ5ጂ ኔትወርክ ዝርጋታ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ፣ አገልግሎቱ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ለማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤ እነርሱም፡-
• አሰላ ዞን አስተዳደር ቢሮ፣
• አሰላ ኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ፣
• አሰላ ስታዲዮም፣
• አሰላ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና
• አሰላ ከቢሮ ትምህርት ቢሮ አካባቢዎች ናቸው፡፡
የዘመናችንን የመጨረሻ እጅግ ፈጣን የሞባይል ኢንተርኔት ግንኙነትን በሺዎች ለሚቆጠሩ ደንበኞች በማቅረብ፣ ፈጣን እንከን አልባ የዳታ ግንኙነትን ከማቅረብ ባሻገር የኢንዱስትሪ ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ለማዘመን ምቹ መደላድል ለመፍጠር ተችሏል።

የ5ጂ ትሩፋት፡ ህይወትንና ኢንዱስትሪዎችን መለወጥ

የ5ጂ ቴክኖሎጂ እስከ 10 Gbps የሚደርስ ፍጥነት ያለው፣ ትእዛዝ የመቀበል ደረጃው (latency) እስከ 1 ሚሊ ሰከንድ የሚደርስ እና ቅጽበታዊ ሲሆን በአንድ ስኩዌር ኪሎ ሜትር እስከ 1 ሚሊዮን የቴሌኮም መሳሪያዎችን የማስተናገድ አቅም አለው። ይህ ቴክኖሎጂ በግለሰቦች፣ በድርጅቶች እና በኢንዱስትሪዎች በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዳታ እና የኢንተርኔት ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል ሲሆን፡-

 ተጨማሪ የኔትወርክ አቅም እና የአገልግሎት ጥራት፣
 አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣
 አስተማማኝ የኦንላይን ትምህርት እና ስልጠና ለማግኘት፣
 ለጀማሪ የንግድ ተቋማት (startups) የላቀ የፈጠራ እና የስራ እድል ፈጠራ
 የዲጂታል ተጠቃሚነት ክፍተትን ለማጥበብ የሚያስችል የዘመናዊ ስልክ አቅርቦትን ለማሳደግ እና የዲጂታል ሊትሬሲን ለመጨመር አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።

የ5ጂ ቴክኖሎጂ ከግል እና ከድርጅት ደንበኞች በተጨማሪ፣ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ላይ ለውጥ የሚያመጡ መፍትሄዎችን/ሶሉሽኖችን ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን እነርሱም፣

ስማርት ጤና፡– የርቀት ምርመራዎች፣ የቀጥታ/ኦንላይን የታካሚ ክትትል እና የቴሌሜዲስን አገልግሎቶች፤
ዘመናዊ ግብርና፡ ስኬታማ ግብርና (precision farming) ፣ ስማርት የመስኖ ዘዴዎች እንዲሁም የግብርና ድሮን ቴክኖሎጂ፤
ስማርት ትምህርት: የኦንላይን ትምህርት (immersive e-learning)፣ የዲጂታል መማሪያ ክፍሎች እና ቤተ-መጻሕፍት፤
ስማርት ማኒፋክቸሪንግ እና ማዕድን፡ ስማርት ፋብሪካዎች፣ አውቶሜሽን እና የኢንዱስትሪ አይኦቲ /ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ/ የበይነመረብ ቁሶች፤
ስማርት ትራንስፖርት፡ ስማርት መጓጓዣ፣ አየር ማረፊያ፣ ሎጂስቲክስ፣ የትራፊክ ቁጥጥር፤
ስማርት መዝናኛ፡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ስትሪሚንግ፣ ኤአር/ቪአር (AR/VR) እና የቀጣይ ትውልድ የክላውድ ጌም ተሞክሮዎችን እውን ያደርጋል።

የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት ማራመድ

5ጂ የንግድ ሥራዎችን ለማዘመን፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና ፈጠራን ለማበረታታት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን ምርታማነትን በማሳደግ፣ ወጪዎችን በመቀነስ እና አዳዲስ የገቢ እድሎችን በመፍጠር፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያደርጋታል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ አገልግሎትን በመላው ሀገራችን በማስፋፋት፣ የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን እና ግለሰቦችን፣ የንግድ ተቋማትን እና ኢንዱስትሪዎችን በቴክኖሎጂ ለማስታጠቅ የሚያደርገውን ቁርጠኛ ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።
ፈጣኑን የኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ ኔትወርክ ይሞክሩ!
ደንበኞች እጅግ ፈጣን የሆነውን የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት በተለያየ አማራጭ ማለትም፣
• በ5ጂ ሞባይል ያልተገደበ ዳታ፣
• 5ጂ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት (5ጂ FWA) እና
• የተለያዩ የ5ጂ ሞባይል ዳታ ጥቅሎች ማግኘት ይችላሉ፤

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በ114 ከተሞች!

ኩባንያችን በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚጠበቅበትን ቁልፍ ሚና አጠናክሮ በመጫወት ዜጎች ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽኖች እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በሁለቱ ሪጅኖች ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የኔትወርክ ማስፋፊያ ሥራ በማጠናቀቅ 114 ከተሞችን የዘመናዊው 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል፡፡

በዚህም መሰረት ኩባንያችን በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ177 ጣቢያዎች ላይ የአቅም ማሳደግ (Upgrade) ስራ በማከናወን እንዲሁም 58 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 56 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት እንዲያጣጥሙ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን በሚከተሉት ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች

አዳባደሎመናሃሮዱቤናኬ ነገዎ
አጋርፋደሎሰብሮሄባኖነገሌ መተማ
አሊደምበል ሄሮሮነገሌ ሲጋዎ
አንጌቱደዴቻሂሱነንሰቦ ጨቢ
አሪዳዲንሳሆማኦቦራ
አሳሳዲንሾጃራኦቦርሶ
ባሌ ጎባዶዶላጂብሪልኦዳ ነጌሶ
ባሌ ሮቤጋሰራኮኮሳራዪቱ
በሂማገረምባቦኮሬሮቤ ገርጀ
ቤሊቱጊንርኩብሳሳልካ
በረ ዲምቱጎሮ ላጆሳንቢቲ
በረድሃረዋ-2መሊዩ ቡርቃሰልካ
ቢድሬሃረዋ አኖሌሚጫ ቢሊሶሶፍ ኦመር
ቦኮሬሃሮ ዱማልሚኦወርቃ

በተመሳሳይ በኩባንያችን ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ227 ጣቢያዎች ላይ አቅም በማሳደግ (Upgrade) በማከናወን እንዲሁም 53 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 58 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በደቡብ ምስራቅ ሪጂን በሚከተሉት ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች

አባጄማቦሎሀሊላቲጮ
አቦምሳቦሩ ጃዊሀሮ አዲተሬታ
አቦሳቡልቡላጎቤሳሶደሬ
አዳሚ ቱሉቡልቻናሁሩታስሬ
አርቦዬጮሌጂዶስልታና
አርሲ ሮቤደርባኬላ ከተማ (አርሲ)ሹኔ
አሴቆዲገሉቀርሳ ከተማ (አርሲ)ሴሩ
አሰላዲክሲስኩላሰዲካ
ባቱ ዶኒኩሉምሳሳጉሬ
ቦቆጂኤጎሎዴ ጂማታኦጎልቾ
ቤሌጋዶ ጉናሎሌ ከተራኔጌሌ የገብያ
ቦፋጎንዴመቂመተሃራ
ቦሌሐቤሜራሮመርቲ
ጡሙጋቲጆስርቦአደሌ (አርሲ)
ኢተያጫንጮ (አርሲ)

ከ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን የዜጎችን የዲጂታል ሊትረሲ ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ላይ ስንሆን ይህም የዜጎችን የዲጂታል ክፍተት በማጥበብ፣ የዲጂታል እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ በከተሞች እና ገጠር እንዲሁም በጾታዎች መካከል ያለውን የዲጂታል ክፍተት (Digital Divide) ለማጥበብ ያስችላል፤ አዳዲስ የስራና ፈጠራ እድሎችን በመፍጠር አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው። ኩባንያችን በቅርቡ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጂን የሚገኙ በርካታ ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በመጨረሻም ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ እና 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም እንደፍላጎት በአገልግሎት ማዕከሎቻችን በማግኘት እጅግ የላቀ ፍጥነት ያለው ኔትወርክ ተጠቃሚ በመሆን አስደናቂ ተሞክሮዎችን እንድታገኙ በደስታ እንጋብዛለን፡፡

                                        የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ላይ!
                                               ሚያዝያ 2 ቀን 2025 ዓ.ም
                                                     ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives