የአየር ሰዓት መሙላት

የቅድመ ክፍያ ሞባይሎን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በቀላሉ የአየር ሰዓት ሞልተው ይጠቀሙ!

ካርድ መፋቅ ሳያስፈልግዎ የአየር ሰዓት ለቅድመ ክፍያ ሞባይልዎ በቀላሉ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ተጠቅመው መሙላት ያስችልዎታል፡፡ ይሙሉ፣ ኤሌክትሮኒክ ቫውቸር (EVD) እንዲሁም ሞባይል ዋሌት ተጠቅመው አየር ሰዓት መሙላት ይችላሉ፡፡

ይሙሉ

  • ለቅድመ ክፍያ ሞባይል ቁጥርዎ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የአየር ሰዓት ከብር 5 እስከ ብር 5,000 መሙላት ይችላሉ፡፡
  • አገልግሎቱን በማንኛውም ሱቆች፣ ሱፐርማርኬቶች እንዲሁም ሌሎች የይሙሉ አገልግሎት የሚሰጡ አጋሮቻችን ጋር በተጨማሪም በሽያጭ ማዕከሎቻችን ያገኛሉ፡

ኤሌክትሮኒክ ቫውቸር ማሰራጨት (EVD)

  • ኤሌክትሮኒክ ቫውቸር ስርጭት ፖስ ማሽንን በመጠቀም በቀላሉ የሞባይል አየር ሰዓት መሸጥ ማለት ነው፡፡

የሞባይል ካርድ ይሸጣሉ? የሚፋቀውን የሞባይል ካርድ መግዛት፣ ማጓጓዝ እንዲሁም ማከማቸት ሳይጠበቅብዎ ለቅድመ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች የፖስ ማሽን በመጠቀም በቀላሉ የኤሌክትሮኒክ ቫውቸር ካርድ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

በሞባይል ዋሌት የአየር ሰዓት የሚሞሉ አጋሮቻችን

በሲቢኢ ብር

  • *847#በመደወል ወደ ሲቢኢ ብር አካውንትዎ ይግቡ
    • የአየር ሰዓት ለመግዛት የሚለውን አማራጭ ከማውጫው ይምረጡ
  • ለራስዎ ለመሙላት
    • ለራሴ ስልክ የሚለውን ይምረጡ
    • የብር መጠኑን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ያረጋግጡ
  • ለሌሎች ለመሙላት
    • ለሌላ ስልክ የሚለውን ይምረጡ
    • የስልክ ቁጥሩን ይፃፉ
    • የብር መጠኑን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ያረጋግጡ
      •  
  • የሲቢኢ ብር ወኪል ለደንበኞች ከታች ባለው መመሪያ መሰረት የአየር ሰዓት መሸጥ ይችላል

    • *847# ይደውሉ
    • የቢዝነስ አገልግሎቱን ይምረጡ
    • የአየር ሰዓት መሸጥ የሚለውን ይምረጡ
    • ስልክ ቁጥሩን ያስገቡ
    • የብር መጠኑን ያስገቡ
    • የኦፕሬተር መለያዎን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ለማረጋገጥ እሺ የሚለውን ያጫኑ

በሲቢኢ የሞባይል መተግበሪያ

    • የሲቢኢ ሞባይል መተግበሪያዎን ይክፈቱ
    • ከሚመጣልዎት አማራጭ ውስጥ አየር ሰዓት ለመሙላት የሚለውን ይምረጡ
    • የአየር ሰዓት ለመግዛት የሚለውን ይጫኑ
    • የሞባይል ቁጥር ያስገቡ
    • የብር መጠን ይፃፉ
    • ያስገቡ የሚለውን ይጫኑ
  • በአጭር ቁጥር *889#
    • *889# ይደውሉ
    • 1 ቁጥር በመምረጥ ወደ አካውንትዎ ይግቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ሌሎች አማራጮች የሚለውን ይምረጡ
    • የአየር ሰዓት ለመግዛት የሚለውን ይምረጡ
    • የሞባይል ቁጥር ይፃፉ
    • የብር መጠን ያስገቡ
    • ያረጋግጡ

ለአዋሽ ባንክ ደንበኞች

  • *901# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • 2 ቁጥር ላይ የሞባይል ቢል የሚለውን ይምረጡ
  • ተቀናሽ የሚደረግበትን የአካውንት ቁጥር ይምረጡ
  • 1 ቁጥር በመጫን የሞባይል ቅድመ ክፍያ ካርድ ለመሙላት የሚለውን ይጫኑ
  • 1 ቁጥር በማስገባት ለራሴ የሞባይል ቁጥር የሚለውን አማራጭ ይጠቀሙ
  • መጠኑን በብር ያስገቡ
  • 1 ቁጥር በመጫን ያረጋግጡ

ሄሎ ካሽ ሞባይል ዋሌት በመጠቀም

  1. ሶማሊ ማይክሮ ፋይናንስ*838*2*4*የአገልግሎት ቁጥር*የገንዘብ መጠን*የሚስጢር ቁጥር#
  2. በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ*983*2*4*የአገልግሎት ቁጥር*የገንዘብ መጠን*የሚስጢር ቁጥር#
  3. ወጋገን ባንክ*819*2*4*የአገልግሎት ቁጥር*የገንዘብ መጠን*የሚስጢር ቁጥር#
  4. አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ*803*2*4*የአገልግሎት ቁጥር*የገንዘብ መጠን*የሚስጢር ቁጥር#

ለህብረት ባንክ (ህብር ሞባይል) ደንበኞች

  • ለራስዎን ሞባይል ቁጥር ለመሙላት
    • *812# ይደውሉ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ከማውጫው ውስጥ “7”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ከማውጫው ውስጥ “1”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንትዎን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • የሚሞሉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን በማስገባት ያረጋግጡ
  • ለሌላ ሞባይል ቁጥር ለመሙላት
    • 812# ይደውሉ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ከማውጫው ውስጥ “7”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ከማውጫው ውስጥ “2”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንትዎን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • የሞባይል ቁጥሩን ይፃፉ
    • የሚሞሉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን በማስገባት ያረጋግጡ

ለብርሃን ባንክ ደንበኞች

  • *881# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥር ያስገቡ
  • 5 ቁጥርን በማስገባት (የቢል ክፍያ) ይምረጡ
  • 1 ቁጥር በማስገባት የአየር ሰዓት ለመሙላት የሚለውን ይምረጡ
  • ለቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ከሆነ 1 ቁጥርን ይመረጡ
  • ለድህረ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ከሆነ 2 ቁጥርን ይመረጡ
  • ተቀናሽ የሚደረግበትን የአካውንት ቁጥር ይምረጡ
  • የሚሞላበትን ሞባይል ተጠቃሚ ይምረጡ
    • ለራስዎ የሚሞሉ ከሆነ 1 ቁጥርን ይስገቡ
    • ለሌላ ሞባይል ተጠቃሚ ለመሙላት ከሆነ 2 ቁጥር ያስገቡ
  • የገንዘብ መጠን ያስገቡ
  • ባለ 6 አሃዝ የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ
  • 1 ቁጥር በመምረጥ ያረጋግጡ

ለአባይ ባንክ ደንበኞች

  • ለራስዎን ሞባይል ቁጥር ለመሙላት
    • *812# ይደውሉ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ከማውጫው ውስጥ “7”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ከማውጫው ውስጥ “1”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንትዎን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • የሚሞሉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን በማስገባት ያረጋግጡ
  • ለሌላ ሞባይል ቁጥር ለመሙላት
    • 812# ይደውሉ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
    • ከማውጫው ውስጥ “7”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ከማውጫው ውስጥ “2”ን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንትዎን በመምረጥ “ይላኩ” የሚለውን ይጫኑ
    • የሞባይል ቁጥሩን ይፃፉ
    • የሚሞሉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
    • የሚስጢር ቁጥርዎን በማስገባት ያረጋግጡ

እናት ባንክ

  • *845# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥር ያስገቡ
  • 4 ቁጥርን በማስገባት (ክፍያ) የሚለውን ይምረጡ
  • 1 ቁጥርን በማስገባት (አየር ሰዓት) የሚለውን ይምረጡ
  • ተቀናሽ የሚደረግበትን የአካውንት ቁጥርዎን ይምረጡ
  • የራስዎን የሞባይል ቁጥር ለመሙላት:

           o 1ቁጥርን በማስገባት (ለራሴን ሞባይል ቁጥር ለመሙላት) የሚለውን ይምረጡ

           o መሙላት የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ

           o 1 ቁጥር በማስገባት ያረጋግጡ ወይም 2 ቁጥር በማስገባት ያቋርጡ

  • ለሌላ የሞባይል ቁጥር ለመሙላት:

           o 2ን በማስገባት (ለሌላ ሞባይል ቁጥር ለመሙላት) የሚለውን ይምረጡ

           o የሚሞላበትን ስልክ ቁጥር ያስገቡ

           o መሙላት የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ

           o 1 ቁጥር በማስገባት ያረጋግጡ ወይም 2 ቁጥር በማስገባት ያቋርጡ

በተጨማሪም የእናት ባንክ የሞባይል መተግበሪያን ከአፕ ስቶር ወይም ከጎግል ፕሌይ ስቶር አውርደው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ለኦሮሚያ ባንክ ደንበኞች

  • *840# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • 3 ቁጥርን በመምረጥ (አየር ሰዓት ለመሙላት) የሚለውን ይምረጡ
  • 1 ቁጥር በመምረጥ (ለራስዎ) የሚለውን በመምረጥ ለራስዎ ሞባይል ቁጥር መሆኑን ያረጋግጡ
    • የሚሞሉት የአየር ሰዓት መጠን ያስገቡ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንት ቁጥርዎን ይምረጡ
    • ለማረጋገጥ 1ቁጥርን ያስገቡ ወይም ለማቋረጥ 2 ቁጥርን ያስገቡ
  • 2 ቁጥር በመምረጥ (ለስጦታ) የሚለውን በመምረጥ ለሌሎች አየር ሰዓት ለመሙላት መሆኑን ያረጋግጡ
    • የሚሞላበትን የሞባይል ቁጥር ያስገቡ
    • የሚሞሉት የአየር ሰዓት መጠን ያስገቡ
    • ተቀናሽ የሚደረግበትን የባንክ አካውንት ቁጥርዎን ይምረጡ
    • ለማረጋገጥ 1ቁጥርን ያስገቡ ወይም ለማቋረጥ 2 ቁጥርን ያስገቡ

ቡና ባንክ ደንበኞች

  • *820# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • ከዝርዝር ውስጥ የአየር ሰዓት የሚለውን ይምረጡ
  • ተቀናሽ የሚደረግበትን የአካውንት ቁጥር ይምረጡ
  • የሚሞሉትን የአየር ሰአት አይነት ይምረጡ
  • የሚሞሉት ለራስዎ ሞባይል ወይም ለሌላ ሞባይል ቁጥር መሆኑን ይምረጡ
  • የሚሞሉት የአየር ሰዓት መጠን ያስገቡ
  • ያረጋግጡ

ኤም ብር

  • *818# ይደውሉ
  • 4 ቁጥርን አማራጭ ይምረጡ
  • 1 ቁጥር በመምረጥ ለራስዎ ሞባይል ቁጥር አየር ሰዓት መሙላት ይችላሉ እንዲሁም
  • 2 ቁጥር በመምረጥ ለሌሎች ሞባይል ቁጥር አየር ሰዓት መሙላት ይችላሉ
  • ከ 1 እስከ 9 ከተዘረዘሩት የአየር ሰዓት የገንዘብ መጠን ውስጥ ምርጫዎትን ያስገቡ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • ለማረጋገጥ 1 ቁጥር ወይም ለማቋረጥ 2 ቁጥር ያስገቡ

ለፀሃይ ሞባይል ባንኪንግ (ሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ) ደንበኖች

  • *873# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • የአየር ሰዓት ለመግዛት የሚለውን አማራጭ ይምረጡ
  • ለራስዎ ሞባይል ቁጥር ለመሙት ለራሴ ቁጥር የሚለውን ይምረጡ
    • የገንዘን መጠን ያስገቡ
    • ያረጋግጡ
  • ለሌላ ቁጥር ለመሙላት
    • የሚሞላበትን የሞባይል ቁጥር ያስገቡ
    • የገንዘን መጠን ያስገቡ
    • ያረጋግጡ

ለኢ-ብር ደንበኞች/ ኢ-ብር ሞባይል ዋሌት

  • *841# ይደውሉ
  • የሚስጢር ቁጥርዎን ያስገቡ
  • 6 ቁጥር በማስገባት የሞባይል ካርድ የሚለውን ይምረጡ
  • 1 ቁጥርን በማስገባት ለራስ የአየር ሰዓት ለመሙላት የሚለውን አማራጭ ይምረጡ
  • የገንዘብ መጠን ያስገቡ
  • 1 ቁጥር በማስገባት ያረጋግጡ

በሞባይል ዋሌት የአየር ሰዓት አጋሮቻችን