ብዙ ክፍያዎችን በአንዴ በቴሌብር መክፈል በማንኛውም ጊዜ የሰራተኞችዎን ደሞዝ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በአንዴ በቀላሉ በመክፈል ጊዜዎንና አላስፈላጊ ወጪዎን ይቆጥቡ። ቴሌብር ድርጅቶች ለደንበኞቻቸውና ወይም ተጠቃሚዎቻቸው በብዛትና በተመሳሳይ ጊዜ ገንዘብ ለማስተላለፍ ያገለግላቸዋል። ድርጅቶች በአንዴ በርካታ ወይም ብዙ ገንዘብ ለማስተገላለፍ ወይም ለመላክ በቅድሚያ ለአገልግሎቱ መመዝገብ እና በአካውንታቸው በቂ ሒሳብ ሊያስቀምጡ ይገባል። መዳረሻመዳረሻ የቴሌብር መላ አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን በቴሌብር ደሞዛቸውን ለሚቀበሉ የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ክሬዲት እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ መላ መዳረሻ ምርት ዝቅተኛ ከፍተኛ የአገልግሎት ክፍያ የክሬዲት መጠን 1000 36000 የመመለሻ ቀነ ገደብ 90 ቀናት ወይም 3 ወር የብድር መክፈያ ጊዜ በየወሩ ከመመለሻ ቀነ ገደብ ወይም ከ90 ቀናት በኋላ 0.5% በቀን ማስታወሻ፡–የብድር ገደብ ከብር 1,000 እስከ 36,000 ነው።የመመለሻ ቀነ ገደብ ከ90 ቀናት በኋላ ይሆናል…. ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑየመዳረሻ ክሬዲት አገልግሎትን ለማግኘት ሰራተኞች በቅድሚያ የውል ስምምነት መፈጸም ይገባቸዋል፡፡ሰራተኞች በ90 ቀናት ውስጥ ብድሩን ከመለሱ የአገልግሎት ክፍያው 10% ይሆናል።ከብድር መክፈያ ቀነ ገደቡ በኋላ ተበዳሪዎች በቀን5% ከጠቅላላው ቀሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል።ደመወዛቸው በቴሌብር ገቢ ሲደረግ የተመላሽ ክፍያው ወዲያውኑ ተቀናሽ/ተፈጻሚ ይሆናል።ሰራተኞች የደሞዛቸውን 30% መበደር ይችላሉ።ከፋይ/ቀጣሪ ድርጅቱ እና እና ሰራተኞች ደሞዛቸውን በቴሌብር ለመቀበል የሚያስችል ስምምት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡የመዳረሻ ብድር አገልግሎትን ለማግኘት ሰራተኞች 3 ጊዜ (ወራት) ደሞዛቸውን በቴሌብር መቀበል ይጠበቅባቸዋል።የኮንትራት ውሉ ሲፈረም የደመወዛቸውን 30% በክሬዲት እንዲወስዱ የሚያስችል ይሆናል።ክሬዲቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ይሆናል፡፡ቀጣሪ ድርጅቱ/ኩባንያው የሰራተኞቹ የደሞዝ ክፍያ በቴሌብር መክፈሉን እንደሚቀጥል በማረጋገጥ እንንሁም ኮንትራቱን ሲያቋርጥ ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮ ቴሌኮም ማሳወቅ አለበት።