የጨረታ ቁጥር – NAAZ/FF/237/22

ኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን አዲስ አበባ ዞን ጽ/ቤት ፈረንሳይ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ላይ የተወሰኑ ክፍት ክፍሎችን ማከራየት በመፈለጉ ለንግድ/ለቢሮ አገልግሎት ለመከራየት ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratenders.com)፣  አፍሮ ቴንደር (www.afrotender.com) እና ቱ መርካቶ ዶት ኮም (www.2merkato.com ) ድህረ ገፅ (web site) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ከተጠቀሱት ድህረ ገፆች የጨረታ ሰነድ በመግዛት ፈረንሳይ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ላይ  የሚከራዩትን ክፍት ክፍሎችን ከጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ማየት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ/ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከሆነ የታደሰ የምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ (በንግድ ስራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ብቻ)

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በክፍያ ማዘዣ ቼክ /CPO/ ብር 10,000.00 ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1243053 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives