የኢትዮ ቴሌኮም የ2013 በጀት ዓመት መጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የሦስት ዓመት ስትራቴጂና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር ተግባራት በማውጣት እና ለውጤታማነቱ አጠቃላይ የተቋሙን ማህበረሰብ በጋራ በማጣመር ኩባንያችን በደንበኞቹ፣ በሠራተኞቹና በአጋሮቹ ዘንድ ተመራጭ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡