ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ሀገር ቤት በመግባት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ልዮ የዲያስፖራ ጥቅል አገልግሎት መስጠት ጀመረ” 

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ጥሪ መሰረት ለአዲስ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡ እና ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮ ቴሌኮም ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎት ማለትም የድምፅ፣ የኢንተርኔት እና አጭር የፅሁፍ መልዕክት ያጣመረ ጥቅል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለፀ:: ኢትዮ ቴሌኮም ያቀረበው ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎት የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ ዝግጅቱን ባጠናቀቀባቸው ሸራተን አዲስ፣ ሂልተን አዲስ አበባ ፣ ኢንተርኮንትኔንታል ፣ ራማዳ አዲስ ፣ ማሪዮት ፣ ካፒታል እና ኢሊሊ ሆቴሎች በቅርቡ ሀገር ቤት ለገቡና በመግባት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል:: በተጨማሪም ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ በሌሎች ሆቴሎች በተመሳሳይ ሁኔታ አገልግሎቱን እንደሚጀምር አሳውቋል:: በቀጣይም ለጎብኚዎች በቋሚነት የሚቀርብ ልዩ አገልግሎት ከጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተቋሙ አመልክቷል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives