የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በ114 ከተሞች!
ኩባንያችን በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚጠበቅበትን ቁልፍ ሚና አጠናክሮ በመጫወት ዜጎች ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽኖች እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በሁለቱ ሪጅኖች ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የኔትወርክ ማስፋፊያ ሥራ በማጠናቀቅ 114 ከተሞችን የዘመናዊው 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል፡፡
በዚህም መሰረት ኩባንያችን በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ177 ጣቢያዎች ላይ የአቅም ማሳደግ (Upgrade) ስራ በማከናወን እንዲሁም 58 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 56 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት እንዲያጣጥሙ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን በሚከተሉት ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች
አዳባ | ደሎመና | ሃሮዱቤ | ናኬ ነገዎ |
አጋርፋ | ደሎሰብሮ | ሄባኖ | ነገሌ መተማ |
አሊ | ደምበል | ሄሮሮ | ነገሌ ሲጋዎ |
አንጌቱ | ደዴቻ | ሂሱ | ነንሰቦ ጨቢ |
አሪዳ | ዲንሳ | ሆማ | ኦቦራ |
አሳሳ | ዲንሾ | ጃራ | ኦቦርሶ |
ባሌ ጎባ | ዶዶላ | ጂብሪል | ኦዳ ነጌሶ |
ባሌ ሮቤ | ጋሰራ | ኮኮሳ | ራዪቱ |
በሂማ | ገረምባቦ | ኮሬ | ሮቤ ገርጀ |
ቤሊቱ | ጊንር | ኩብሳ | ሳልካ |
በረ ዲምቱ | ጎሮ | ላጆ | ሳንቢቲ |
በረድ | ሃረዋ-2 | መሊዩ ቡርቃ | ሰልካ |
ቢድሬ | ሃረዋ አኖሌ | ሚጫ ቢሊሶ | ሶፍ ኦመር |
ቦኮሬ | ሃሮ ዱማል | ሚኦ | ወርቃ |
በተመሳሳይ በኩባንያችን ደቡብ ምስራቅ ሪጂን የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ ለማስፋፋት በ227 ጣቢያዎች ላይ አቅም በማሳደግ (Upgrade) በማከናወን እንዲሁም 53 አዳዲስ ጣቢያዎችን በመገንባት 58 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በደቡብ ምስራቅ ሪጂን በሚከተሉት ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች
አባጄማ | ቦሎ | ሀሊላ | ቲጮ |
አቦምሳ | ቦሩ ጃዊ | ሀሮ አዲ | ተሬታ |
አቦሳ | ቡልቡላ | ጎቤሳ | ሶደሬ |
አዳሚ ቱሉ | ቡልቻና | ሁሩታ | ስሬ |
አርቦዬ | ጮሌ | ጂዶ | ስልታና |
አርሲ ሮቤ | ደርባ | ኬላ ከተማ (አርሲ) | ሹኔ |
አሴቆ | ዲገሉ | ቀርሳ ከተማ (አርሲ) | ሴሩ |
አሰላ | ዲክሲስ | ኩላ | ሰዲካ |
ባቱ | ዶኒ | ኩሉምሳ | ሳጉሬ |
ቦቆጂ | ኤጎ | ሎዴ ጂማታ | ኦጎልቾ |
ቤሌ | ጋዶ ጉና | ሎሌ ከተራ | ኔጌሌ የገብያ |
ቦፋ | ጎንዴ | መቂ | መተሃራ |
ቦሌ | ሐቤ | ሜራሮ | መርቲ |
ጡሙጋ | ቲጆ | ስርቦ | አደሌ (አርሲ) |
ኢተያ | ጫንጮ (አርሲ) |
ከ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን የዜጎችን የዲጂታል ሊትረሲ ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ላይ ስንሆን ይህም የዜጎችን የዲጂታል ክፍተት በማጥበብ፣ የዲጂታል እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ በከተሞች እና ገጠር እንዲሁም በጾታዎች መካከል ያለውን የዲጂታል ክፍተት (Digital Divide) ለማጥበብ ያስችላል፤ አዳዲስ የስራና ፈጠራ እድሎችን በመፍጠር አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው። ኩባንያችን በቅርቡ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጂን የሚገኙ በርካታ ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በመጨረሻም ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ እና 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም እንደፍላጎት በአገልግሎት ማዕከሎቻችን በማግኘት እጅግ የላቀ ፍጥነት ያለው ኔትወርክ ተጠቃሚ በመሆን አስደናቂ ተሞክሮዎችን እንድታገኙ በደስታ እንጋብዛለን፡፡
የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ላይ!
ሚያዝያ 2 ቀን 2025 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም