ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ላይ

በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮም እና ዲጂታል አገልግሎቶች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡ ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ኢትዮ ቴሌኮም የሀገራችን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ጥረት አካል ሲሆን፣ በመላ ሀገሪቱ አስተማማኝ፣ እንከን አልባ እና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ ለአዳዲስ ፈጠራዎች እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አዳዲስ ዕድሎችን ይከፍታል።

ኩባንያችን በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ. በ2022 ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የ5ጂ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ በመላ ሀገሪቱ ወደሚገኙ ከተሞች እያስፋፋ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ድረስ፣ ጅማን ጨምሮ በ12 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ እና በቢሾፍቱ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።

በጅማ ከተማ የተጀመረው የ5ጂ አገልግሎት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጭው ጊዜ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተደራሽነት ለመጨመር ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።

5 አገልግሎት በጅማ  

በጅማ ከተማ በመከናወን ላይ የነበረው የ5ጂ ኔትወርክ ዝርጋታ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ፣ አገልግሎቱ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ለማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤ እነርሱም፡-

  • የጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣
  • የደቡብ ምዕራብ ኢትዮ ቴሌኮም ጽ/ቤት፣
  • ፈረንጅ አራዳ፣ ሴንትራል ሆቴል፣ ኃይሌ ሆቴል እና ስታዲየም፣
  • ዶሎሎ ሆቴል፣ ፍሮምሲስ ሆስፒታል እና መርካቶ መካከል፣
  • ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ ቆጪ፣ ሚዛን እና ቦዬ አካባቢዎች ሲሆኑ፣

የዘመናችንን የመጨረሻ እጅግ ፈጣን የሞባይል ኢንተርኔት ግንኙነትን በሺዎች ለሚቆጠሩ ደንበኞች በማቅረብ፣ ፈጣን እንከን አልባ የዳታ ግንኙነትን ከማቅረብ ባሻገር የኢንዱስትሪ ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ለማዘመን ምቹ መደላድል ለመፍጠር ተችሏል።

5 ትሩፋት፡ ህይወትንና ኢንዱስትሪዎችን መለወጥ

የ5ጂ ቴክኖሎጂ እስከ 10 Gbps የሚደርስ ፍጥነት ያለው፣ ትእዛዝ የመቀበል ደረጃው (latency) እስከ 1 ሚሊሰከንድ የሚደርስ እና ቅጽበታዊ ሲሆን በአንድ ስኩዌር ኪሎ ሜትር እስከ 1 ሚሊዮን የቴሌኮም መሳሪያዎችን የማስተናገድ አቅም አለው። ይህ ቴክኖሎጂ በግለሰቦች፣ በድርጅቶች እና በኢንዱስትሪዎች በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዳታ እና የኢንተርኔት ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል ሲሆን፡-

  • ተጨማሪ የኔትወርክ አቅም እና የአገልግሎት ጥራት፣
  • አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣
  • አስተማማኝ ኦንላይን ትምህርት እና ስልጠና ለማግኘት፣
  • ለጀማሪ የንግድ ተቋማት (startups) የላቀ የፈጠራ እና የስራ እድል ፈጠራ
  • የዲጂታል ክፍትን ለማጥበብ የሚያስችል የዘመናዊ ስልክ አቅርቦት ለማሳደግ እና የዲጂታል ሊትሬሲን ለመጨመር አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።

የ5ጂ ቴክኖሎጂ ከግል እና ከድርጅት ደንበኞች በተጨማሪ፣ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ላይ ለውጥ የሚያመጡ መፍትሄዎች ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን እነርሱም፣

  • ስማርት ጤና፡- የርቀት ምርመራዎች፣ የቀጥታ/ኦንላይን የታካሚ ክትትል እና የቴሌሜዲስን አገልግሎቶች፤
  • ዘመናዊ ግብርና፡ ስኬታማ ግብርና (precision farming)፣ ስማርት የመስኖ ዘዴዎች እንዲሁም የግብርና ድሮን ቴክኖሎጂ፤
  • ስማርት ትምህርት: ኢ-ትምህርት (immersive e-learning)፣ የዲጂታል መማሪያ ክፍሎች እና ቤተ-መጻሕፍት፤
  • ስማርት ማንዩፋክቸሪንግ እና ማዕድን፡ ስማርት ፋብሪካዎች፣ አውቶሜሽን እና የኢንዱስትሪ አይኦቲ፤
  • ስማርት ትራንስፖርት፡ ስማርት መጓጓዣ፣ አየር ማረፊያ፣ ሎጂስቲክስ፣ የትራፊክ ቁጥጥር፤
  • ስማርት መዝናኛ፡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ስትሪሚንግ፣ ኤአር/ቪአር (AR/VR) እና የቀጣይ ትውልድ የክላውድ ጌም ተሞክሮዎችን እውን ያደርጋል።

የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት ማራመድ

5ጂ የንግድ ሥራዎችን ለማዘመን፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና ፈጠራን ለማበረታታት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን ምርታማነትን በማሳደግ፣ ወጪዎችን በመቀነስ እና አዳዲስ የገቢ እድሎችን በመፍጠር፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ተወዳዳሪ ያደርጋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ አገልግሎትን በመላው ሀገራችን በማስፋፋት፣ የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን እና ግለሰቦችን፣ የንግድ ተቋማትን እና ኢንዱስትሪዎችን በቴክኖሎጂ ለማስታጠቅ የሚያደርገውን ቁርጠኛ ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።

ፈጣኑን የኢትዮ ቴሌኮም 5 ኔትወርክ ይሞክሩ!

ደንበኞች እጅግ ፈጣን የሆነውን የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት በተለያየ አማራጭ ማለትም፣

  • በ5ጂ ሞባይል ያልተገደበ ዳታ፣
  • በ5ጂ ሞባይል ያልተገደበ ዳታ፣
  • 5ጂ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት (5G FWA) እና
  • የተለያዩ የ5ጂ ሞባይል ዳታ ጥቅሎች ማግኘት ይችላሉ፤

በመጨረሻም ክቡራን ደንበኞቻችን በዚህ አጋጣሚ የ5ጂ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም እንደፍላጎት በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የእጅግ ፈጣኑን ኔትወርክ ተጠቃሚ በመሆን አስደናቂ ተሞክሮ እንድታገኙ በደስታ እንጋብዛለን፡፡

የካቲት 10፣ 2017 ..
ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives