ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አስጀመረ!

ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡ የዲጂታል መታወቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኩባንያችን በወር በአማካይ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ለ32 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ ዕቅዱን 36% የሚያከናውን ይሆናል፡፡ ለዚህም ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላትን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን ስራውን አስጀምሯል፡፡ በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በሌሎች ከተሞች ማስፋፊያ የሚያከናውን ይሆናል፡፡

 የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ ከዜጎች በሚወሰዱ ውስን የባዮሜትሪክስ እና ዲሞግራፊክ መለያ አማካይነት የተረጋገጠ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ለቀልጣፋ ለአካታች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለቢዝነስ ትስስር፣ ለኢ-ጋቨርመንት አገልግሎት፣ በዳታ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርአት ለመገንባት፣ ለቀልጣፋ ማህበራዊ አገልግሎት፣ ለተሻለ የዜጎች ህይወት እንዲሁም የሳይበር ማጭበርበርን በመከላከል አስተማማኝ የዲጂታል ሥነምህዳር ለመፍጠር የላቀ ሀገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ ምርትና አገልግሎት ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮ እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስ ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነት የሚጨምሩ የማይክሮ ብድር አገልግሎቶች ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡ በሀገራችን የተማከለ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዳታቤዝ መገንባት ለቢዝነስ እና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈጣን እና አስተማማኝ የማንነት ማረጋገጫ (authentication) በመስጠት የተሻለ አሰራርን እንዲተገብሩ የሚያስችል ነው፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጋ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላቱን፣ ምርት እና አገልግሎቱን በአጋርነት የሚያቀርቡ ፍራንቻይዝ ማዕከላቱን፣ ወኪሎቹን እንዲሁም የገነባውን ግዙፍ የዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ሰርቪስ እና የዲጂታል መሰረተልማት አስቻይ ሁኔታ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያከናወኑ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያቸውን ባሉበት ሆነው ዳታ ብቻ በማብራት በነጻ በቴሌብር ሱፐርአፕ አማካይነት በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭ አመቻችቷል፡፡

እድሜያቸው ከአምስት አመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን በኩባንያችን ይፋ በተደረጉት የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ቀበሌ መታወቂያ፣ የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወዘተ ያሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ የሚችሉ ይሆናል፡፡ ከከተማ እና ገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና የብሔራዊ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ በተለያዩ የተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና ሌሎች በሀገራችን የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ እና ሪጅኖች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላቶቻችን የሚከተሉት ሲሆኑ በቀጣይም በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት እና ወኪሎቻችን ይከናወናል፡፡

አዲስ አበባ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅን
ውሃ ልማት   (ሃያ ሁለት) አቃቂ ሐረር ጎንደር ወልቂጤ
ልደታ ጀሞ ደብረብርሀን አዘዞ ጅማ
ስታዲየም ለቡ ፊቼ መቀሌ(ሁለት) ቦንጋ
ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተል ለገጣፎ ባሕርዳር ሚዛን
ገርጂ አራዳ አምቦ ዓባይ   ማዶ ጋምቤላ
አያት ኮልፌ ሰበታ አዳማ ነቀምቴ   እና
ስድስት ኪሎ ቡራዩ   እና ጅግጅጋ ቢሾፍቱ አሶሳ
ጉርድ ሾላ ቲፒኦ   (ጥቁር አንበሳ) ድሬዳዋ ሐዋሳ(ሁለት)
ሽሮሜዳ ሰመራ ሻሸመኔ
ሳሪስ ደሴ ወላይታ   ሶዶ

ዜጎች ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን በአቅራቢያቸው የሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በቀላሉ ለማግኘት ቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ የሚገኘውን የ National ID Registration Locator መተግበሪያ መጠቀም ወይም ድረገጻችንን www.ethiotelecom.et መጎብኘት ይችላሉ፡፡

   ኢትዮ ቴሌኮም

 ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም.   

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives