የኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ የስትራክቸር ስራ ተጠናቀቀ፡፡ በዚህም የአጠቃላይ ግንባታ ስራው 58.95 በመቶ መጠናቀቁና በዉል በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡
መስከረም 19 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ግንባታው በሚከናወንበት ስፍራ በመገኘት ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ግንባታዉን በሚያከናውነው የCGCOC Group እና በአማካሪ ድርጅቱ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኃላ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አቶ አማረ አሰፋ ህንፃው የኢትዮ ቴሌኮምን ፍላጎት፣ የሰራተኛውን እድገት እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተከትሎ የተገነባ መሆኑን ገልፀው በዋናነት ለሰራተኛው የተሻለ የመስሪያ አካባቢ ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጎ ግንባታው መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
አቶ አማረ አክለውም ግንባታው የተቋሙ ስትራቴጅ አክል መሆኑንና የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንትም የግንባታውን ሂደት በቅርበት ክትትል እያደረገ መሆኑንና በዚህም ጥሩ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ዋና አርክቲክት ኢንጅኔር ዳንኤል አለማየሁ በበኩላቸው ህንፃው በአምስት ብሎኮች የተዋቀረና በውስጡ እስከ 5 ሽህ ሰራተኞችን የመያዝ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋ፡፡ ህንፃው ከቢሮዎች በተጨማሪ የተለያየ መጠን ያላቸው አዳራሾች፣ ቤተ-መፅሃፍ፣ ጂምንናዚየም፣ መዝናኛዎችና ካፊቴሪያዎች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ፍሲሊቲዎች እንደሚኖሩት ኢንጅኔር ዳንኤል ተናግረዋል፡፡
ከ4.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአይ.ሲ.ቲ መንደር ውስጥ የሚገነባው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ ስራ ለመስራት CGCOC Group ከተባለ የውጭ የግንባታ ኩባንያ ጋር ነሐሴ 14 ቀን 2008 ስምምነት ተደርጎ ወደስራ የተገነባ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ህዳር ወር ላይ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ርክክብ ለማድረግ ውል መያዙ ይታወሳል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
መስከረም 19 ቀን 2011 ዓ.ም
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ የስትራክቸር ስራ ተጠናቀቀ
Share This Post:
Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin